በጆን ሆምስ የቅንጦት ሪል እስቴት ደንበኞቻችን ምርጡን ሊገባቸው ይገባል ብለን እናምናለን። ቤት ለመግዛትም ሆነ ለመከራየት ከፈለጉ ሁሉንም የሪል እስቴት ኩባንያዎችን በአንድ ቦታ እናቀርባለን። የእኛ ድረ-ገጽ የተነደፈው የት እንደሚገዙ ወይም እንደሚከራዩ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ እንዲያደርጉ ለመርዳት ነው፣ በዚህም ለፍላጎትዎ እና ለበጀትዎ ተስማሚ የሆነ ንብረትዎን ማግኘት ይችላሉ። ሁሉንም የሪል እስቴት ኩባንያዎቻችንን በአንድ ቦታ ከመዘርዘር በተጨማሪ የትኛው የተሻለ እንደሆን በጆን ሆምስ ባለሙያዎች ጥሩ የሚባል መረጃ ያገኛሉ።
ተልዕኮ
የእኛ ተልእኮ ሰዎች የተሻለውን የወደፊት ቤት እንዲያገኙ መርዳት ነው - ከዚያም በፍላጎታቸው እና በምርጫዎቻቸው ላይ በመመስረት ምርጥ አማራጮችን በመስጠት ህልማቸውን እንዲያገኙ መርዳት ነው።
ራዕይ
እ.ኤ.አ በ2030 ለደንበኞቻችን ምርጥ የሪል እስቴት መድረክ እንሆናለን። የእኛ መድረክ አስተማማኝ እና ምቹ አገልግሎቶችን ይሰጣል, በዚህም ለደንበኞቻችን ዋጋ ይሰጣል።
ውድ ደንበኞቻችን
ድርጅታችን ጆን ቴክ ሶሉሽን በ2013 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን የተለያዩ የሶፍትዌር፤ የዌብሳየት እንዲሁም የአይሲቲ ስራዎችን እየሰራ ህብረተሰቡን እያገለገለ ይገኛል። ጆን ቴክ ሶሉሽን በስሩ ጆን ሆምስ የተሰኘ የሪል ስቴት ማሻሻጫ (PROPERY LISTING) ሲስተም ገንብቶ አጠናቋል።
ጆን ሆምስ በአይነቱ ለየት ያለ ዌብሳይት ገንብቶ ደንበኞች ያሰኛቸውን ሪልስቴት የሚመለከቱበት እንዲሁም የሚገበያዩበትን ዘመናዊ ሲስተም ነው። የጆን ሆምስ ዋና አላማ ደንበኞች ሁሉንም የሪልስቴት ቤት አማራጮች በአንድ ቦታ አማርጠው የሚመለከቱበት ዌብሳይት ሲሆን ትክክለኛ መረጃዎችን እንዲያገኙም ይረዳቸዋል።
ጆን ሆምስ ቅድሚያ ለተገልጋዮች በመስጠት ደንበኞቻችን ምንም አይነት መጉላላት ሳይደርስባቸው መብታቸው ተጠብቆ እንዲሁም በሪልስቴት ድርጅቶች ከሚደርስባቸው እንግልት ሙሉ በሙሉ በሚያስብል ደረጃ ተቀርፎ ደንበኞች ተደስተው የወደፊት ቤታቸውን የሚያገኙበትን ሲስተም አዘጋጅተን ጨርሰናል።
ደንበኞች በመጀመሪያ የወደዱትን ቤት ሲስተማችን ላይ ገብተው ይመርጣሉ። ሲስተማችን ላይ የቤቱን አቀማመጥ፣ ቦታ (Location)፣ ፍሎር ፕላን (Floor Plan)፣ዋጋ፣ የብድር አገልግሎቶች ፣ሰፋ ያሉ ተጨማሪ የተለዩ ነገሮችን እና የመሳሰሉትን ማግኘት ይችላሉ። የወደዱትን ቤት ሲመርጡ የጆን ሆምስ ባለሙያዎች በተለያየ የመገናኛ መንገዶች(ዘዴዎች) ያገኟቸዋል። ለጊዜው በዱባይ፣ በጀርመን፣ በአሜሪካ የሚገኙ ኤጀንቶች ስላሉን የበለጠ ነገሮችን ቀላል ያደርግልናል።
የወደዱትን ቤት አይተው ሙሉ ማብራሪያ አግኝተው እንዲሁም ከጆን ሆምስ መሀንዲስ ባለሙያዎች ስለቤቱ አቀማመጥ፣ የሚሰራበትን ዕቃዎች (ማቴሪያልስ) እና የመሳሰሉትን መረጃዎች ከሌሎች የሪልስቴት ቤቶች ጋር አነፃፅረው ለደንበኞች ያቀርባሉ። በተጨማሪም የጆን ሆምስ የኢኮኖሚክስ ባለሙያዎቻችን ደግሞ ስለቤቱ የወደፊት ሁኔታ ማለትም ቢሸጥ ወይም ቢከራይ ምን ያህል ሊያወጣ እንደሚችል፣ ከአመት አመት ሊኖረው የሚችለውን የዋጋ ትንበያና የመሳሰሉትን በመተንበይ ደንበኞች የትኛው የተሻለ እንደሆነ በቀላሉ መገንዘብ ይችላሉ።
ጆን ሆምስ ከሪልስቴት ድርጅቶች ጋር አብሮ ቢሰራም በገለልተኝነት ለየትኛውም የሪልስቴት ድርጅት ሳይወግን የሚሰራ ድርጅት ነው፡፡ ጆን ሆምስ ወደፊት የሚኖረውን የዋጋ ትንበያ እንዲሁም የሪልስቴት ድርጅቱ የሚያዋውለውን አይቶ መርምሮ የደንበኛውን መብት ጠብቆ የተሻለ ቤት በተሻለ ዋጋ እንድንገዛ የሚያደርግልን ሲስተም ነው።
በጆን ሆምስ መገበያየት የሚያስገኙን ዋና ዋና ጥቅሞች፡
1. ደንበኞች በሪልስቴት ድርጅቶች መታለልን ሙሉ በሙሉ በሚያስብል ደረጃ የሚቀንስ በመሆኑ።
2. የተለያዩ ቋንቋዎችን በውስጡ ያካተተ በመሆኑ።
3. ሁሉንም የሪልስቴት ቤቶችን በአንድ ቦታ፣ በቤቶዎ ሆነው በቀላል መንገድ ግብይት መፈፀም እዲቻል በማረጉ።
4. በጆን ሆምስ መሃንዲሶች ስለቤቱ አቀማመጥ፣ የሚሰራበትን ማቴሪያል፣ የትኛው ሪልስቴት የተሻለ ቦታዎች (Location) ላይ እንደሚገኝ እና የመሳሰሉትን መረጃዎች ከሌሎች የሪልስቴት ቤቶች ጋር አነፃፅሮ ማማከሩ።
5. በጆን ሆምስ ኢኮኖሚስቶች ወደፊት የተሰራበት ቦታ ላይ ምን ያህል እድገት እንደሚኖር፣ ለመሸጥ ወይም ለማከራየት ቢፈለግም ምን ያህል ሊያወጣ እንደሚችል፣ በአጠቃላይ ወደፊት ሊኖረው የሚችለውን ይዞታ ከሌሎች የሪልስቴት ቤቶች ጋር አነፃፅሮ ማስቀመጡ እና የመሳሰሉት